Implementation Plan for the Continuation of Vital Health Services during COVID-19 Pandemic by the Ministry of Health
Date posted: Saturday, April 4, 2020
በቻይና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ (COVID 19) ከተከሰተበት ታህሳስ 31 2019 እ.ኤ.አ ስርጭቱ በተለያዩ የአለማችን ሀገሮች ላይ ተስፋፍቶ የጎላ ጉዳቶችን በማስከተል ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ መሰረት ከዚህ ወደ ከፋ ሂደት ዉስጥ እንዳንገባ ሀገራችን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተሩ የሚመራ በተዋረድም ይንን ወረርሽኝ ለመከላከል እየተሰራ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአንፃራዊ ሁኔታ ዝቅተኛ ቢሆንም የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ምርምር ኢንስትቱት ከሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና የክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር ከፍተኛ የሆነ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ የማሕበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥም የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሩን እና የመገናኛ ብዙሐንን ባሳተፈ መልኩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ማለትም “ደጋግሞ እጅን መታጠብ እና ከብዙ ሰዎች/ቡድን ጋር አለመገናኘትን ጨምሮ” ህዝቡ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
መንግሥት የህብረተሰቡን ተጋላጭነት ከመቀነስ አንፃር ከወሰዳቸው እርምጃዎች መካከል የተጠርጣሪዎች እና ታማሚዎች የተለየ የህክምና ስፍራ ማዘጋጀት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 80 መዳረሻዎች የሚጓዙ በረራዎችን ማገድ፤ ከጎረቤት አገሮች ጋር ድንበር መዝጋት እና ለወረስሽኙ የሚሆን የሐብት እና ግብአት ማሰባሰብ ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ተጋላጭ የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች ከቤት የሚሰሩበት መንገድ የተመቻቸ ሲሆን ስርጭቱን የሚያባብሱ ስብሰባዎች እና ሌሎች ሰዎች ሊሰባሰቡባቸው የሚችሉ ተግባራትም ታግደዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ወረርሽኙ እንደ ኤርትራ፣ ኬንያ ፣ ጅቡቲ ፣ ሶማሊያ፤ ሱዳን እና ኡጋንዳ ያሉ የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን ጨምሮ በአብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ታይቷል፡፡
ተጨማሪ ከበታች ያለውን የPDF FILE ያንብቡት
FOLLOW US ON
X